በዚህ እጅግ ውብ በሆነው የተማሪዎች ምርቃት ላይ ክቡር ዶክተር ደረጀ ዱጉማ የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታና የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ፣ክቡር አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ የኢፌዴሪ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ፣ክቡር ዶክተር ብርሀነ መስቀል ጠና ፣ፕሮፌሰር ጌትነት ታደለ፡ የፕሮፌሰሮች ካውንስል አባልና የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ ም/ሰብሳቢ እንዲሁም የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ አባላት በተገኙበት እጅግ ደማቅ በሆነ መልኩ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎቹን በማስመረቅ ላይ የሚገኝ ሲሆን ክቡር ዶክተር ፋሪስ ደሊል የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ በዓመቱ ውስጥ በመማር ማስተማር ፣በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ያካተተ ንግግር አድርገዋል፡፡ ክቡር ዶክተር ደረጀ ዱጉማ የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ እና የዕለቱ የክብር እንግዳ በፕሮግራሙ መዝጊያ ላይ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በዚህ የምርቃት ፕሮግራም ላይ በመጀመሪያ ዲግሪ ወንድ 1002 ሴት 429 ድምር1431 በሁለተኛ ዲግሪ ወንድ 51 ሴት 13 በድምሩ 64 በአጠቃላይ ወንድ 1053 ሴት 442 ድምር 1495 ተማሪዎች በመመረቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
ላይ የጉራጌ የባህል ኪነት ቡድን ኢትዮጵያዊ አንድነትን የሚገልጹ ልዩ ልዩ ጣዕመ ዜማዎችን በማቅረብ የመድረኩ ድምቀት ሆነዋል፡፡ በድጋሚ ውድ ተመራቂዎቻችንና የተመራቂ ተማሪዎቻችን ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ::