ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄደውን የኬሮድ ስፖርት ማህበር ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ለ”ኢትዮጵያ ሰላም እንሩጥ” በሚል መሪ ቃል ሰኔ 19/2014 ዓም መነሻውን ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በማድረግ በወልቂጤ ከተማ ይጠናቀቃል፡፡ ውድድሩ የዩኒቨርሲቲያችንን ገጽታ በማስተዋወቅ፣ መልካም ማህበራዊ ግንኙነታችንን በማጠናከር እንዲሁም በስፖርቱ በመሳተፍ ጤንነታችንን ከመጠበቅ አንጻር ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል፡፡ ስለሆነም የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ በሙሉ በንቃት እንዲሳተፍና የፕሮግራሙ ድምቀት እንዲሆን ከወዲሁ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡