የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ እና የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት የተከበሩ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ በዛሬው ዕለት በዩኒቨርሲቲው በመገኘት የዩኒቨርሲቲውን የስራ እንቅስቃሴ የጎበኙ ሲሆን ተቋሙን አስመልክቶ ሰፊ የሆነ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡ ለተከበሩ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የማኔጅመንት አካላት የተከናወነ ሲሆን የጉብኝት ሂደቱ የተከናወነው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋሪስ ደሊልን ጨምሮ ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ሲሆን የተከበሩ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ የጎበኙዋቸው ዋና ዋና ቦታዎች የዩኒቨርሲቲውን ዋናውን ግቢ፣ቤተሙከራዎችን ፣ቤተመጽሀፍት፣ የተማሪዎች ማደሪያ፣ የሶስተኛው ዙር የኮቪድ 19 ክትባት ሂደት፣የተለያዩ በጅምር ላይ ያሉ ግንባታዎችና የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ሲሆን በተለይም የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ