ለውይይቱ መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋሪስ ደሊል ሲሆኑ በመነሻ ጽሁፋቸው ላይ ሀገራችን ኢትዮጵያ ባሳለፈቻቸው የለውጥ ዓመታት ከእያንዳንዱ ለውጥ የተማርናቸውን መሰረታዊ ነጥቦችን ከየተግዳሮቶቻቸው ጭምር በማጣመር በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ በተለይም ባለፉት አራት የለውጥ ዓመታት ያሰተዋልናቸውን በጎ ጅምሮችና ያጋጠሙን ተግዳሮቶችን በመዘርዘር ከቀድሞ ጉድለቶቻችን ተምረን በተለይም የተሰበረውን መጠገን ይገባናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም የለውጡ ትሩፋቶችና ያጋጠሙን ችግሮች፤ በሀገረ ለውጡ የወጣቱና የልሂቃኑ ሚናነን በዝርዝር ገልጸዋል ::
ዶክተር ፋሪስ አያይዘውም በችግሮቻችን ላይ በግልጽ በመነጋገር ምን ማድረግ ይጠበቅብናል? የሚል ጥያቄ አዘል ሃሳብ ካነሱ በኋላ ጥያቄውን መሰረት በማድረግ በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ማተኮር እንዳለብን በስፋት አብራርተዋል፡፡
- የዜጎችን ሰላምና ደህንነት የማረጋገጥ ጉዳይ
- ህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን የመገንባት
- የኑሮ ውድነትን የማቃለል አማራጮችን አሟጦ የመጠቀም
- ለስራ አጥነት ችግር የጋራ መፍትሄ የማስቀመጥ
- ከመንግስት አገልግሎት ጋር በተያያዘ የሚታይ የመልካም አስተዳደር ችግርን በጋራ የመፍታት
- ለልማት ጥያቄዎቻችን ምላሽ ምቹ ሁኔታዎችን የመፍጠር
- የተገራ ሚዲያና የኮሙኒኬሽን ስራ
በቀረበው የመነሻ ጽሁፍ ዙሪያ ተሰብሳቢዎች የተለያዩ አስተያየቶችን ያቀረቡ ሲሆን በዋናነት ትኩረት ያደረጉባቸው ነጥቦች፡-
Ø የህግ የበላይነትን ከማስከበር አንጻር
Ø የጸጥታ መዋቅሩ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች
Ø ከመልካም አስተዳደር አንጻር ያሉ ችግሮች
Ø ከኑሮ ውድነት አንጻር ያሉ ችግሮች በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን በተነሱት ነጥቦች ዙሪያ የተከበሩ አቶ መሀመድ ጀማል የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና ዶክተር ፋሪስ ደሊል በቀረቡት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ዙሪያ ምላሽና ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል፡፡