የአቀባበል ስነስርዓቱ ከማለዳ ጀምሮ በመከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን ለቅበላው አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶች መደረጋቸውን ከቅበላ ኮሚቴው ለማረጋገጥ ችለናል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ነባር ተማሪዎች በተማሪዎች ህብረት አማካይነት ተቀናጅተው በፍጹም ትህትና እና የፍቅር ስሜት ወንድምና እህቶቻቸውን በመቀበል ላይ ይገኛሉ፡፡
ውድ ተማሪዎቻችን የሠላም ተምሳሌት ፤የአብሮነት መገለጫ፤ የፍቅር አብነት ወደ ሆነው በታታሪውና በስራ ወዳዱ ማህበረሰብ ዙሪያውን ታጅቦ ወደሚገኘው የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እንኳን በሠላም መጣችሁ እያልን የትምህርት ቆይታችሁም ያማረና የሰመረ እንዲሆንላችሁ ከወዲሁ ልባዊ ምኞታችንን እንገልጻለን።
ማስታወሻ
የማደሪያ ክፍል ድልደላን በተመለከተ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ድህረ-ገፅ {wkusu.com} ላይ ስለተለቀቀ የብሄራዊ ፈተና አድሚሽን ቁጥር (Admission Number) በማስገባት ዶርም ቁጥር እና ህንፃ ቁጥር ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
በተጨማሪም ድህረ-ገፁ ላይ አድሚሽን ቁጥር ስታስገቡ ሙሉ ስም ከመጣላችሁ የመኝታ ህንፃና ክፍል ወደ ቀኝ በማድረግ ማየት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።