የመግባቢያ ስምምነቱን በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እና በ“South Omo Theatre Company, UK.” መካከል የተከናወነ ሲሆን በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በኩል ስምምነቱን የፈረሙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር ፋሪስ ደሊል ሲሆኑ በ“South Omo Theatre Company, UK.” በኩል ስምምነቱን የፈረሙት ቤን ያንግ ናቸው፡፡ ስምምነቱ ሁለቱን ተቋማት በቴአትርና አርት፤ በፊልምና በተዛማች የምርምር ስራዎች በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸው ነው፡፡
በመግባቢያ ሰነዱ ላይ እንደተገለጸው የስምምነቱ ዋነኛ ዓላማ በሀገር በቀል ዕውቀት ላይ መሰረት ያደረጉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ያላቸውና ተወዳዳሪ የሆኑ ቴአትሮችን፤ዘጋቢ ፊልሞችን ፤ የምርምር ስራዎችን ሁለቱ ተቋማት በትብብር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸው እንደሆነ ተገልጿል፡፡