የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የሥራ አመራር ቦርድ ሆነው ከሚያዝያ 01/2014 ዓ.ም ጀምሮ እንዲያገለግሉ
- ክቡር ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ የኢፌዴሪ ጤና ሚስቴር ሚንስትር ዴኤታ……ሰብሳቢ
- ፕሮፌሰር ጌትነት ታደለ፡ የፕሮፌሰሮች ካውንስል አባል…………………ም/ሰብሳቢ
- ክቡር አቶ መሀመድ ጀማል፡ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ……….……….………. አባል
- ፕሮፌሰር ገዛኸኝ በሬቻ፡ የፕሮፌሰሮች ካውንስል አባል…………………………. አባል
- አቶ አብርሀም አላሮ፡ የብርሃን ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ……….……….……… አባል
- አቶ ኤርሚያስ እሸቱ የንግድ ምክር ቤት አባል ……………….……….……….… አባል
- ዶ/ር ካሳሁን ተስፋዬ ከምርምር ኢንስቲትዩት ……………….……….…………..አባል
አድርጎ መሰየሙን ለዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ስለሆነም ለአዲሶቹ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ፡ ም/ሰብሳቢ እንዲሁም አባላት በሙሉ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው ዩኒቨርሲቲው እየተመኘ ቀደም ሲል በተለያዩ ጊዜያት ዩኒቨርሲቲውን በሥራ አመራር ቦርድ አመራርነት ሲያገለግሉ ለነበሩት አመራሮች በሙሉ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ዩኒቨርሲቲው የከበረ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ