ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ነባር ቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም ለሁሉም የዩኒቨርሲቲው ነባር ቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች የትምህርት ምዝገባ የሚከናወነው እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
- ሁሉም ነባር ሶስተኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ቅድመ ምረቃ እንዲሁም አዲስና ነባር የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የመመዝገቢያ ጊዜ ጥቅምት 28 እና 29/2015 ዓ.ም ሲሆን ትምህርት የሚጀመረው ጥቅምት 30/2015 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በየኮሌጃችሁ ሬጅስትራር በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
- ነባር አንደኛ ዓመት ( Freshman) ተማሪዎች የትምህርት ክፍል ምደባ ገለጻ (Orientation) የሚሰጠው ጥቅምት 28/2015 ዓ.ም ሲሆን ወደ ትምህርት ክፍል መግቢያ ፈተና ጥቅምት 29/2015 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ ፡-
ይህንን የመግቢያ ጊዜ አሳልፎም ሆነ ቀድሞ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት