ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

 

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ-ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታችሁ ለመማር ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው ግንቦት 03 እና 04 ቀን 2014 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን በማሟላት በአካል በመገኘት በተጠቀሱት ቀናት ብቻ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለን፡፡

1ኛ) ከስምንተኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያጠናቀቃችሁበት ሙሉ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁ (ሠርተፊኬትና ትራንስክሪብት) ዋናውንና ፎቶ ኮፒ

2ኛ) አራት ፓስፖርት መጠን ያላቸውን ፎቶ ግራፎች፤ 

3ኛ) ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ

ማሳሰቢያ፡-

  • በ2013 ዓ/ም 1ኛ ሴሚስተር በውጤታችሁ መሠረት ዳግም ቅበላ የተፈቀደላችሁ ተማሪዎች በተጠቀሱ ቀናት እንድታመለክቱ እናሳስባለን፤

                                                                                                              የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት!!