ማስታወቂያ

ለሪሚዲያል (REMEDIAL) ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን  የሪሚዲያል (REMEDIAL)  ትምህርት ፈላጊዎችን ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

Read more ...

ለሥልጠና ፈላጊዎች በሙሉ

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) ዳይሬክቶሬት በሥሩ ባሉት በCISCO እና በHuawei ዓለም አቀፍ አካዳሚዎቹ አማካኝነት ሥልጠናዎችን በማታ እና በሳምንቱ መጨረሻ (ቅዳሜና እሑድ) መርሐ ግብር በአነስተኛ ክፍያ ለመሥጠት ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ ስለዚህ ከዩኒቨርሲቲው ውጭ ያላችሁ የማኅበረሰብ አካላት በመመዝገብ ሥልጠናው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

Read more ...

ማስታወቂያ

ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ነባር ቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ

Read more ...

ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ነባር ቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ

 

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም ለሁሉም የዩኒቨርሲቲው ነባር ቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች የትምህርት ምዝገባ የሚከናወነው እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

  1. ሁሉም ነባር ሶስተኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ቅድመ ምረቃ እንዲሁም አዲስና ነባር የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የመመዝገቢያ ጊዜ ጥቅምት 28 እና 29/2015 ዓ.ም ሲሆን ትምህርት የሚጀመረው ጥቅምት 30/2015 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በየኮሌጃችሁ ሬጅስትራር በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
  2. ነባር አንደኛ ዓመት ( Freshman) ተማሪዎች የትምህርት ክፍል ምደባ ገለጻ (Orientation) የሚሰጠው ጥቅምት 28/2015 ዓ.ም ሲሆን ወደ ትምህርት ክፍል መግቢያ ፈተና ጥቅምት 29/2015 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ ፡-

ይህንን የመግቢያ ጊዜ አሳልፎም ሆነ ቀድሞ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

                                                       የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

Copyright © 2023. Wolkite University. Designed by Wolkite University ICT