ማስታወቂያ

National Exit Model Examination Schedule

National Exit Model Examination Schedule of Examinees assigned in Wolkite University. Students who need account activation can go to Central Library starting from tomorrow  morning

Read more ...

ማስታወቂያ

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባቹህ የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ፣

Read more ...

በ2016 ዓ.ም በሀገር-አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን Graduate Admission Test (GAT) የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ያለፋችሁ የድህረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

በ2016 ዓ.ም በሀገር-አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን Graduate Admission Test (GAT) መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ትምህርት ሚኒስቴር በወሰነው መቁረጫ ነጥብ መሰረት ማለፋችሁን ያረጋገጣችሁ

Read more ...

 

በግብርና እና በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ኮሌጅ በwild Life & Ecotourism Management ትምህርት ክፍል አማካይነት ተዘጋጅቶ ከጉራጌ ዞን ከሁሉም ወረዳዎች ለተውጣጡ የቱሪዝም ባለሙያዎችና የዕምነት አባቶች በቱሪዝም ልማት ፤ቅርስ አጠባበቅ /አያያዝ ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና ከታህሳስ 13/2014ዓም ጀምሮ በመሰጠት ላይ ይገኛል ፡፡ ስልጠናው ካዘጋጀው ከwild Life & Ecotourism Management ትምህርት ክፍል መረዳት እንደተቻለው ስልጠናው ለቀጣይ ቀናት ቀጥሎ የሚውል ሲሆን ስልጠናው በሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ እንደሚያተኩር ስልጠናውን ካዘጋጁት ክፍሎች ለመረዳት ተችሏል፡-

  1. ቅርስን እንዴት ማቆየት ይቻላል
  2. የቅርስ አያያዝና አመዘጋገብ ስርዓት በተለይም የሚዳሰሱና የማይዳሰሱትን በመለየት የመመዝገብ
  3. የቅርስ ጥበቃ ስራ አሁናዊ ቁመናው ምን እንደሚመስል
  4. የቱሪዝም ልማትን ይበልጥ ለማጠናከር በተለይም የመስቀልና አረፋ የመሳሰሉትን የቱሪዝም መስዕብ የሆኑ በዓላትን ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ጎብኚዎች መዳረሻ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያስችል አሰራሮችን ይበልጥ ለማጠናከርና በቱሪዝም መዳረሻዎች ላይ ያሉ ችግሮችን በመቅረፍ ዘላቂ የሆኑ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ የሚያስችል ስልጠና መሆኑን ከስልጠናው አዘጋጆች ለመረዳት ተችሏል