ማስታወቂያ

National Exit Model Examination Schedule

National Exit Model Examination Schedule of Examinees assigned in Wolkite University. Students who need account activation can go to Central Library starting from tomorrow  morning

Read more ...

ማስታወቂያ

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባቹህ የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ፣

Read more ...

በ2016 ዓ.ም በሀገር-አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን Graduate Admission Test (GAT) የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ያለፋችሁ የድህረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

በ2016 ዓ.ም በሀገር-አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን Graduate Admission Test (GAT) መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ትምህርት ሚኒስቴር በወሰነው መቁረጫ ነጥብ መሰረት ማለፋችሁን ያረጋገጣችሁ

Read more ...

 

ስነስርዓቱን በንግግር የከፈቱት የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር ፋሪስ ደሊል ሲሆኑ እሳቸውም በንግግራቸው ላይ እንደገለጹት የጉራጌ ዞን አምባሳደር የሆነው የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ከእድሜው አንጻር ሲታይ እጅግ በፈጠነ የዕድገት ቁመና ላይ የሚገኝ ሲሆን በስፖርቱ ዘርፍ የአካባቢውን ማህበረሰብ በማገዝ ላይ ያለ በመሆኑ ይበልጥ ለማጠናከር የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የራሱን ድርሻ መወጣት እንዳለበት ዕምነታቸውን ገልጸዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ አክለውም ይህንን ድጋፍ ለማድረግ የተቋሙ ማኔጅመንት ከመከረ በኋላ ክለቡን ይበልጥ ለማጠናከር በትብብር መስራት አስፈላጊ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ከውስጥ ገቢው ላይ የ3,000,000 (ሶስት ሚሊዮን ብር) ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ታምራት ታየ ዩኒቨርሲቲው ያደረገው ድጋፍ ክለቡን ይበልጥ የሚያበረታታ እና የሚያጠናክረው ነው በማለት ተቋሙን አመስግነዋል፡፡

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን የገለጹት የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ እንዳለ ገ/መስቀል ሃገራችን ላይ ካሉ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አንዱ የሆነውን የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በባለቤትነት ስሜት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሻገር እየተደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ ነው ሲሉ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ከንቲባው አክለውም ዩኒቨርሲቲው ከገንዘብ ድጋፉ ባሻገር ሌሎች ድጋፎችን እንዲያደርግ ጥሪ በማስተላለፍ ዛሬ የተደረገው ድጋፍም ክለቡን ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት ክለቡን ለመደገፍ ከዞኑ የመሰረተ ልማት ወጭዎች ይቀናነስ የነበረ ሲሆን ይህ ድጋፍም የዞኑ ወጭ ከማገዝ አንጻር ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ጋር በቀጣይ በጋራ አብረው ለመስራት የሚያስችል ሁሉን አቀፍ የድጋፍ ውል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በፊት በአካባቢው ለሚገኙ የታዳጊ ስፖርት ክለቦች የትጥቅ ድጋፍ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡