• Registration

መስናና ብልሹ አሠራርን በመከላለከል የህብረተሰቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ የደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አሳሰበ፡፡

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት የተቀናጀ ተቋማዊ የሙስና መከላከል ስትራቴጂ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሠጥቷል፡፡

በደቡብ ብሄር፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የፊት ለፊት የስነ-ምግባር ትምህርትና ስልጠና ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ጋሻዬ ግዛው ስልጠናውን በሠጡበት ወቅት እንደገለፁት ሙስናና ብልሹ አሠራር ትልቁ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲ ግንባታ እንቅፋት ከመሆናቸውም በላይ ለተገልጋይ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዳይሠጥና የሚመደበው የመንግስት ሀብትና ንብረት በአግባቡ ለታለመለት ዓላማ እንዳይውል ያደርጋል ብለዋል፡፡

ስልጠናው በተቋማት ውስጥ አንድ ወጥ ወይም የተቀራረበና የተቀናጀ የሙስና መከላከል ስትራቴጂን ለማዘጋጀት የሚያስችል አቅም እንደሚፈጥር አቶ ጋሻዬ ተናግረዋል፡፡

ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል በዋናነት በመልካም ሥነ-ምግባርና በሙስና አስከፊነት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በስፋት ከማከናወን በተጨማሪ የሥነ-ምግባር አውታሮችን ማደራጀትና ማብቃት፣ ለሙስናና ብልሹ አሠራር የሚያጋልጡ አሠራሮችን በጥናት በመለየት መፍትሄዎችን ፈልጎ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

ሌላው በሙስና ፅንፀ-ሃሳብ ላይ ስልጠና የሠጡት በኮሚሽኑ የፊት ለፊት የስነ-ምግባር ትምህርትና ስልጠና ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ተገኝ ላቀው በበኩላቸው በሀገራችን የተጀመረው የልማት፣ የዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር ግንባታ እንዲሁም የህዳሴው ጉዞ በሙስና እንዳይደናቀፍ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

የስልጠናው ተሳታፊዎች በሠጡት አስተያያት ስልጠናው በሙስና ፅንፀ-ሃሳብና በተቀናጀ ተቋማዊ የሙስና መከላከል ስትራቴጂ ላይ ግንዛቤያቸውን እንዳሳደገላቸው ገልፀው በቀጣይ በየተቋማቸው ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት በትኩረት እንደሚሠሩ ተናግረዋል፡፡

በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው የጉራጌ ዞን አስተዳደር፣ የ13ቱ ወረዳዎችና 2 የከተማ አስተዳደር የሥነ-ምግባር ኦፊሠሮች እንዲሁም ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ የስራ ክፍሎች የተውጣጡ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

                                                                                                                                                  ዘገባው የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

Copyright © 2018. Wolkite University. Designed by Wolkite University ICT

Login Form

Register