የስርዓተ ጾታ ጉዳዮችና ኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ዳይሬክቶሬት

ዳይክቶሬቱ በዩኒቨርሲቲው ተግባሮች ውስጥ የስርዓተ-ፆታ ፍትሀዊነት እንዲረጋገጥ ለማስቻል እና የማህበረሰቡን ህልውና ከሚጎዳው ሰደድ እሳት ለመታደግ  ላለፉት አራት አመታት ከሌሎች የስራ ክፍሎች ጋር በጋራ እየተንቀሳቀሰ ቆይቷል፡፡

የስርዓተ ጾታ ጉዳይና ኤች አይ ቪ/ኤድስ መከ/መቆ/ዳይሬክቶሬት ዋነኛ አላማ በዩኒቨርሲቲ ውስጥና  በአካባቢው የሚገኘውን  ህብረተሰብ ለጾታዊ ትንኮሳ እና ለስነተዋልዶ ጤና እና ኤች አይ ቪ/ኤድስ በሽታ አጋላጭ የሆኑትን ጎጂ ተግባራትን እንዲወገዱ በማድረግ ጤናማ የሆነ፣ ብቁ፣ታታሪ እና የነገ አምራች ዜጋ መፍጠር ነው፡

ዳይሬክቶሬቱ በዋነኝነት የሚያከናውናቸው ተግባራት

 • የስርዓተ ጾታ ፍትሃዊነትን በሁሉም ዘርፍ ማረጋገጥ፣
 • የጾታዊ ትንኮሳ መመሪያዎችን ለህ/ሰቡ ማስገንዘብ፣
 • በሚፈጠሩ የጾታ ትንኮሳዎች ላይ ተገቢው የህግ ድጋፍ እንዲኖር ማድረግ፣
 • የፆታዊ ትንኮሳ ተጎጂዎች ምክርና ድጋፍ የሚያገኙበት ማዕከል በማመቻት አገልግሎቱ መስጠት፣
 • ሴት ተማሪዎች በኢኮኖሚ ችግር ሳቢያ ሊደርስባቸው የሚችሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የፈንድ ማፈላለግ ስራ በመስራት ለ600 ያህል ሴት ተማሪዎች የገንዘብና የፅዳት እቃዎች ድጋፍ መስጠት፣
 • የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ስልቶችን በመቀየስ መስራት፣
 • በቫይረሱ ምክንያት ለተጎዱ የዩኒቨርሲቲው ውስጥና  ከግቢው ውጪ ለሚገኙ ወገኖች መድሎና መገለልን እንዳይደርስባቸው  አስፈላጊውን ድጋፍና እንክብካቤ ማድረግ፣
 • የስርዓተ ጾታ ጉዳይ እና አካል ጉዳተኞችን በማጤን በጾታዊ  ግንኙነት የሚፈጠሩ ችግሮችን  መለየት እና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ፣
 • በስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች ሳቢያ ለሚከሰቱ የጤና እክሎች ከምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ባለድርሻዎችና ከጤና ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር መስራት፣
 • ለማህበረሰቡ የሜይንስትሪሚንግ ስራዎችን ማከናወን፣
 • በስርዓተ ፆታ እና ኤች አይ ቪ ጉዳይ ላይ የሚሰሩ የተማሪዎች ክበባትን በመደገፍ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጥ ተግባራት መስራት፣
 • ሴቶችን በተለየ ሊያበረታታ፣ ሊደግፍና የሴቶችን ድምፅ ሊያሰማ የሚችል የፒጃማ ምሽት በየሳምንቱ ማዘጋጀት፣
 • የሴት ተማሪዎች እና ሴት ሰራተኞች  ፎረም በግቢው ውስጥ በማቋቋም የሴቶችን የአመራር ብቃት ማጎልበት፡፡

የስራ ክፍሉ ሰራተኞች መረጃ

ተ.ቁ

ስራ መደብ

ጾታ

የት/ት ደረጃ

1

የስርዓተ ፆታ ጉዳዮችና ኤች አይ ቪ/ኤድስ መከ/መቆ/ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

ዲግሪ

2

የስርዓተ ፆታ ባለሞያ

ዲግሪ

3

የስነ ልቦና ምክርና ድጋፍ ሰጪ ባሞያ

ዲግሪ

4

የኤች አይቪ/ኤድስ መከ/መቆ/ባለሞያ

ዲግሪ

5

መረጃ አቀባይ

10+1

 

ጠቅላላ ድምር

5

 

 

 

Contact

ICT WKU
ICT Director
Wolkite University
Wolkite, 07
Ethiopia
+251113220131
Mobile: +251912104211
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
Scroll to top